1ኛ፡ ሰው፡-ወዳጄ2ኛ፡ሰው፡- አቤት

1ኛ፡ሰው፡- ያው የተለመደ ወጋችንን እናድርስ

2ኛ፡ ሰው፡- ሸጋ ብለሃል፡፡ በላ ዝለቀው

1ኛ፡ ሰው፡- ደግ አድምጥ

በላ ልበልሃ

የጥንት ስርዓቱን የመሰረቱን ልንገርሃ

ስላሴዎች ስንት ናቸው

እልሃለሁ ምን ትላለህ

2ኛ፡ ሰው፡- ዝግጁ ነኝ ለጥያቄህ

ደግሞ ይቺ ትጠፋኛለች ብለህ

ሶስት ናቸው ልጥቀስልህ

የአራት ኪሎው የእንጦጦውና የደብረ ብርሃን

ብዬሃለሁ ምን ትላለህ

1ኛ፡ ሰው፡- ኽ——————ኽ———–ኽ

እንዴት ቀልደኛ ነህ

ማነው እንዲህ ያስተማረህ

በቁጥር ልክ ብትሆንም

አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ በስም

ገባህ ጃል

2ኛ፡ ሰው፡- በል አድምጥ

ኃይለኛ ነው አሰጋገሩ

በፈረስ ተቀምጦ ማማሩ

ትልቁን አውሬ ደራጐኑን

በጦር ወግቶ መግደሉን

ስለ ታሪኩ ልንገርህ

ስሙን ግን ታውቀዋለህ

1ኛ፡ ሰው፡- አይኼ ይህቺ ትጠፋኛለች ብለኽ ነው

እርሱማ ጊዮርጊስ ነው የአንድማጣው

2ኛ፡ ሰው፡- አንድማጣውን አስቀረው

1ኛ፡ ሰው፡- በል አድምጥ

ሺህ በክንñ ሺህ በአክናñ

አቤት ሲያስፈራ ከነሰይñ

ለቀረቡት የሚራራ

ላቃለሉት እሣቶ ገሞራ

የሚያደርግ ድዳ ሲናደድም

ከእቶን ያወጣል ከእሣትም

ብዬሃለሁ ምን ትላለህ

2ኛ፡ ሰው፡- እርሱማ ወዳጄ ደጉ አባቴ

ገብርኤል ነው ያለው ከፊት ለፊቴ

1ኛ፡ ሰው፡- አሁንስ አግኝተሃል

2ኛ፡ ሰው፡- በላ ልበልሃ

የጥንት ስርዓቱን የመሰረቱን ልንገርሃ

ትውልዳቸው ኢትዮጱያዊ

ምግባራቸው ለብሃዊ

ፃድቅ ናቸው የታወቁ

ክንፍ ለመታደል የበቁ

ብዬሃለሁ ማን ትላለህ

1ኛ፡ ሰው፡- አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ

እልሃለሁ እኔ ደግሞ

2ኛ፡ ሰው፡- ኽ————-ኽ———ኽ

ሃገር ስጠኝ ለስተትህ

ትክክሉን መልስ እንድነግርህ

1ኛ፡ ሰው፡- ኢትዮጱያን በሙሉ ሰጠሁህ

2ኛ፡ ሰው፡- ኢትዮጱያን በሙሉ ገዝቼ

ሃይማኖትን አስፋፍቼ

ጣኦት አምላኪን አጥፍቼ

እኖራለሁ በአምላኬ በርቼ

ተክልዬ ናቸው ደጉ አባታችን

1ኛ፡ ሰው፡- ለዛሬው ይበቃናል

ከብቶቼን ረሣኋቸው አይደል

ከሰው ማሳ ገብተው

በአፈላማ እንዳይዟቸው

በል ወዳጄ ደህና ሰንብት /ነይ ተመለሽ ኡሽሽ———– ተመለሽ/

/ይሄዳሉ/

ይትባረክ አምላከ አበዋነ!!

ትርጉም »