ገብርሔር

6ተኛ ሳምንት ትውስታ የቃሉ ትርጉም ገብር ሥራ፣ ሠራተኛ፣ አገልጋይ ማለት ሲሆን፤ ሔር ደግሞ ቸር፣ መልካም፣ ታማኝ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በሳምንቱ ውስጥ የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ሁሉ ታማኝ አገልጋይ መሆንን ስለሚያመለክት ገብር ሔር በማለት  ስለ ታማኝ አገልጋይ ይሰበክበታል፡፡ ይህን ስብከት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰበከው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ማቴ 25፡14-25)፡፡ በዚህ ሳምንት ባለሥልጣን

ገብርሔር Read More »

ደብረ ዘይት

6ተኛ ሳምንት ትውስታ ደብረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ ዛፍ የበቀለበት ተራራ ሲሆን፣ በዚህ ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ምልክቱ የነገረበት ስለሆነ ስያሜውን ያገኘው ከዚህ ነው (ማቴ 24፡3) ቤተ ክርስቲያንም ለምእመናን የዘመኑን መቅረብ ከምልክቶቹ ጋር በማነጻጸር ታስተምርበታለች፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት ስለ ሐሳዊ መሲህ መምጣት፤ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙ ሰዎች በስሙ

ደብረ ዘይት Read More »

መጻጉዕ

የ4ኛው ሳምንት ትውስታ መጻጉዕ ማለት ድውይ፣ ሕሙም በሽተኛ ማለት ሲኾን፣ በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱን ይታወስበታል፡፡  መነሻ ታሪክ አድርገን የምናስታውሰው የሠላሳ ስምንት ዓመቱን በሽተኛ ቢኾንም (ዮሐ 5፡5-10) ከእርሱ ጋር የተፈወሱትን ሁሉ ይታወሱና የጌታ አዳኝነት በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን (ማቴ 8፡1-4)፣ ዕውር ማብራቱን (ዮሐ 9፡1-11)፣ አንካሶችን ማርታቱን

መጻጉዕ Read More »

ምኩራብ

የ3ኛው ሳምንት ትውስታ ምኵራብ የጸሎት ቤት ማለት ነው፡፡ በዚህ በጸሎት ቦታ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነበባሉ፣ ትምህርትም ይሰጥባቸዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቦታው ይገኝ እንደነበር ወንጌል “በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ” (ማር 1፡21) ይላል፡፡ እርሱ አስቀድሞ በነቢያት “ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ” (ሐጌ 1፡8) እንዳለ እንዲሁ በመመለኪያው ቦታ እጅግ

ምኩራብ Read More »

ስለ ጾም ጠቃሚ ምክር

ጾም ማለት ከእግዚአብሔር የታዘዘ እውነተኛ ሕግ ነው፡፡ ነገር ግን የሥራውን ፍሬ መጀመሪያ እንገልጻለን ጾም ማለት መጀመሪያ ዓይናችን ክፉ ነገርን እንዳያይ፤ ጆሮአችን ክፉ ነገርን እንዳይሰማ፤ አንደበታችን ክፉ እንዳይናገር መከልከል ነው እንጂ እንዲያው ሥጋና ቅቤን ብቻ መተው አይደለም፡፡ መቼም የሰው ባሕርይ በዚህ ዓለም ሲኖር ሁል ጊዜ በደስታና በተድላ ለመኖር ነው የሚጥረው፤ ይኸውም ለሰው ልጅ ሐሳብ ሁለት መንገድ

ስለ ጾም ጠቃሚ ምክር Read More »

ቅድስት

የ2ኛው ሳምንት ትውስታ በሁለተኛው ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም የሚጀምርበት ዋዜማ ስለኾነ እርሱ የጾመው ጾም ቅድስት ጾም መኾኑን የሚሰበክበት ወቅት ነው፡፡ ቅድስት ማለት የተለየች ማለት ነውና፡፡ ዐቢይ ጾም መባሉም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ ልዩ እና ታላቅ የኾነው አምላካችን ጾሙን ጾሞ፣ እንድንጾም ፍለጋውን የተወልን በመኾኑ  በአጠቃላይ ክርስቲያን ኹሉ በአዋጁ ጾም በቤተ ክርስቲያን በመገኘት፣ ቅዳሴ በማስቀደስ፣

ቅድስት Read More »

ዘወረደ

የ1ኛው ሳምንት ትውስታ በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስቦት እኛን የጠፋነውን በጎቹን (የሰው ልጆችን) ፍለጋ  ከሰማየ ሰማያት መውረዱን የምናስታውስበት ነው፡፡  የፍቅር አምላክ ቀጠሮውን ሳያፋልስ ለሰው ልጆች በሰጠው የ5500 ዘመን ፍጻሜ ሲደርስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደልን (ገላ 4፡4)፡፡ ይህን ዘመን ብዙዎች ሊያዩ ተመኝተው “እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ” (ዘፍ 49፡8) እያሉ ዐረፍተ ዘመን

ዘወረደ Read More »

“ቃል ሥጋ ሆነ”

“ቃል ሥጋ ሆነ” (ዮሐ. ፩፥፲፬/1፥14) በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችን እና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችኁ ይህ ቃል ሥጋ የመኾን ምስጢር፡- እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ (ሰው በመሆኑ) [አምላክ ሰው የሆነበት] ልዩ ምስጢር፣ የሰው ልጅ በበደሉ ምክንያት ከመጣበት ሞት የዳነበት ምስጢር፣ ቤተ ክርስቲያናችን “ተዋሕዶ” የሚለውን

“ቃል ሥጋ ሆነ” Read More »

Scroll to Top