ጾመ ሐዋርያት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

‘‘ጾም’’ በፊደላዊ ትርጕሙ ‘ጾመ’ ተወ፣ ታቀበ፣ ታረመ፣ ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ነው፤ የቃሉም ፍቺ ምግብን መተው፣ መከልከል፣ መጠበቅ ማለት ነው፤ ስለዚኸም ጾም ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች፣ በቤተ ክርስቲያን የሥርዐት መጻሕፍት ከተወሰነው ጊዜ ሳያጓድሉ፣ መከልከል፤ ወይም ለተወሰነ ጊዜ እና ሰዓት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ኹሉ መወሰን (መታቀብ) ማለት ነው፤ ለሰውነት የሚያምረውን እና የሚያስጎመዠውን ነገር ኹሉ፣ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ መተውም ነው፡፡…

በእምነታቸው ምሰሉአቸው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

`በእምነታቸው ምሰሉአቸው`
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው” (ዕብራ. 13፡7) ባለው መሠረት እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የአባቶቻችንን የሐዋርያትን እምነት በመምሰል እነርሱ እንደጾሙት የእመቤታችን የፍልሰትዋን መታሰቢያ በየዓመቱ እንጾማለን፡፡