እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴ 28፥19

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት

መደበኛ ጉባኤ

በእምነታቸው ምሰሉአቸው` ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው” (ዕብራ. 13፡7) ባለው መሠረት እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የአባቶቻችንን የሐዋርያትን እምነት በመምሰል እነርሱ እንደጾሙት የእመቤታችን የፍልሰትዋን መታሰቢያ በየዓመቱ እንጾማለን፡፡

ብሒለ-አበው

ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው፡፡ ቅዱስ ስራፕዮን * የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡ መጽሐፈ ምክር * አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ * ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡ ማር ይስሐቅ

ተምሮ ሬድዮ

ተምሮ ማስተማር ሬድዮ በተለያዩ መርሐ ግብሮች የያዘ ሲሆን ከያዙት መርሐ-ግብሮች ውስጥ ስብከት፣መዝሙር፣ትረካ እና የመሳሰሉ ሲሆን ይህ የሬድዮ መርሐ-ግብር ሳምንት በሳምንት አዲስ የሚለቀቅ ሲሆን የሚለቀቀው በዩቲየብ ሲሆን በድምጽ ብቻ ይለቀቃል፡፡www.youtub.com/temromastemar

ትርጉም »